Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

hsema

Homeland Security and Emergency Management Agency
 

DC Agency Top Menu

-A +A
Bookmark and Share

መረጃ ይኑሮት

የአስቸኳይ ግዜ የመጀመሪያው ነገር መረጃ ማግኘት ነው፡፡ በዙሪያዎ ምን እየተከሰተ እንዳለ ካወቁ በቤተሰብዎ እና በሚወዷቸው ደህንነት ላይ ውሳኔ ለማድረግ የተሸለ እድል አለዎት፡፡ ለቀው ይወጣሉ ወይስ በመጠለያ ይቆያሉ? የወተትና ዳቦ ወይም የፕላስቲክ ጨርቅና ፕላስተር ክምችት ያስፈልጎታል? ቀጠናው የተለያዩ መርጃዎች ለነዋሪዎች እንዲደርስ ያደርጋል፣ መመዝገብ ወይም መከታተል ብቻ ይጠበቅቦታል፡፡

  • ለአለርት ዲሲ ይመዝገቡ፡- ተመዝግበው በኢማይል ወይም በሞባይል ስልክዎ በጽሁፍ መልዕክት /ኤስኤምኤስ ማሳሰቢዎች ለመቀበል Alertdc.dc.gov ይብኙ፡፡
  • የቴሌቪዥን ዜና ይከታተሉ፡- የቲቪ ጣቢያ 13፣ 16 ወይንም በአካባቢዎ የዜና ጣቢያ ላይ በማድረግ ማሳሰቢያዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ያግኙ፡፡
  • ሬዲዮ ያድምጡ፡ የዲስትሪክቱ መንግስት የሚሰጠዉን ይፋዊ መረጃ እና መመሪያ የሚያሰራጨዉን የአከባቢዉ ሬዲዮ ጣቢያ ይፈልጉ፡፡
  • የድንገተኛ ጊዜ ማሳሰቢያ ስርአት፡.የድንገተኛ ጊዜ ማሳሰቢያ ስርአት(ኢኤኤስ) ብሄራዊ የህዝብ ማሳሰቢያ ስርአት ነው፡፡ ድስትሪክቱ በኢኤኤስ አማካይነት እንደ አምበር ማሳሰቢያዎች እና የአየር ሁኔታ መረጃ ያሉ ጠቃሚ የድንገተኛ ክስተት መረጃን ለአካባቢ በሚሰራጪ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ የኬብል ቴሌቪዥን ስርአት ፣ገመድ አልባ ኬብል ስርአት ፣ሳተላይት ዲጂታል ኦዲዮ፣ ሬዲዮ አገልግሎት አቅራቢዎች እና በቀጥታ ስርጭት ሳተላይት አማካይነት መረጃ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ቀጠናው የንግድ ሞባይል ማስጠንቀቂያ ሲስተምን በመጠቀም የአስቸኳይ ግዜ ማስጠንቀቂያ በቀጥታ በተንቀሳቃሽ ስልኮች መላክ ይችላል፡፡
  • 911 ግልባጭ ፡የድንገተኛ ጊዜ ሰራተኞች ስለድንገተኛ ሁኔታ ሊያሳውቅዎ እና እራስዎን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳልብዎት ለእርስዎ ለመንገር ስልክ እንዲደውሉልዎ ያስችላችዋል ፡፡ በዲስትሪክቱ ዉስጥ ያሉት መደበኛ ስልኮች ሁሉም በአዉቶማቲክ ይመዘግባሉ፡፡
  • ማህበራዊ ሚዲያ ፡- ኤችኤስሲኤምኤን በ Twitter በ @DC_HSEMAላይ ይከተሉ እንዲሁም የ Facebook ገጻችንን ላይክ በ facebook.com/HSEMADC ላይ ላይክ ያድርጉ፡፡